የሙስና መንስኤ ምንድነው?

ሙስና በኢትዮጵያ አብዝቶ መንሠራፋቱንና ለዚህም ምክንያት ከሆኑ ጉዳዮች መካከል የሲቪክ ማኅበራት በነፃነት መንቀሣቀስ አለመቻል፣ የመናገርና የፕሬስ ነፃነት መገደብ፣ የሕዝባዊ ተሣትፎ ማነስ እና የመንግሥት ለሕግጋት ተገዥ አለመሆን እንደሚገኙበት አንዳንድ ምሁራን ገልፀዋል፡፡ ፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥት ሙስናን ለመከላከል የያዘው ጥረት አበረታች መሆኑንና በዚህ ጥረት ዙሪያም ዜጎች ሁሉ መሣተፍ እንደሚኖርባቸው ተነግሯል፡፡ በኢትዮጵያ ሙስና ምን ይመስላል? ምንጩ የት ይገኛል? መፍትሐውስ ምን ይሆን? ዓለምአቀፉ ፀረ-ሙስና ጥምረት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ባወጣው በአውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር የ2012 ዓ.ም የሃገሮች የሙስና ሠንጠረዥ ላይ ከተፈተሹት ከ174 ሃገሮች ኢትዮጵያ በ33 ነጥብ 113ኛ ቦታን ይዛለች፡፡ የአፍሪካ የሙስና ገፅታ እአአ በ2012 ዓ.ም የአፍሪካ የሙስና ገፅታ እአአ በ2012 ዓ.ም ከፍተኛውን የመገምገሚያ ነጥብ 90 ያገኙት የተሻሉ ናቸው ተብለው አንደኛ ቦታን የተቆናጠጡት ዴንማርክ፣ ፊንላንድ እና ኒውዚላንድ ሲሆኑ ዝቅተኛው ስምንት ነጥብ የተሰጣቸው ደግሞ የከፋ ሙስና አለባቸው የተባሉት በሠንጠረዡ ግርጌ በ174ኛነት የሠፈሩት አፍጋኒስታን፣ ሰሜን ኮሪያ እና ሶማሊያ ናቸው፡፡ 2.3.ከተጠያቂነት ጋር የተያያዙ ምክንያቶች
ተጠያቂነት ከሌለ ማንም ሰዉ ያሻዉንና የፈቀደዉን እንዲሰራ ምክንያት ይሆናል፡፡አንድ ሰዉ ያሻዉን ሲሰራ የማይጠየቅ ወይም ቁጥጥር የማይደረግበት ከሆነ ደግሞ ሙስና ይከሰታል፡፡
3. የሙስና ወንጀል ልዩ ባህሪያት፣
ወንጀል በአንድ ተወሰነ የህብረተሰብ የእድገት ደረጃ እንደተፈጠረና ከህብረተሰብ እድገት ጋር እያደገና እየተወሳሰበ እንደመጣ ይታመናል፣በተለይም በአዉሮፓ ከነበረዉ የኢንዱስትሪ አብዮት ቦኋላ ከዚህ በፊት ከሚታወቁት ወንጀሎች ሌት ያሉ ወንጀሎች እንደተፈተሩ ነገራል፣የሙስና ወንጀልም ከነዚህ አንዱ ነዉ፡፡ የሙስና ወንጀል ነባር ከሚባሉት የወንጀል አይነቶች (ለምሳሌ ስርቆት፣ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈር ወዘተ.) የተለየና ዉስብስብ እንደሆነ ይገለጻል፡፡የዚህን ወንጀልን ከሌሎች የተለመዱ ወይም ነባር ወንጀሎች የተለየ የሚያደርጉትን ልዩ ሁኔታዎች ማወቅ ሙስና ወንጀልን ለመመርመር፣ለማጋለጥ፣ለመመርመር፣ለመክስስና እጥፊዎችን ለመቅጣት አስቸጋሪ እንዲሆን የሚያደርጉትን ሁኔታዎች ለመረዳትና የተለየ ስልት ለመቀየስ ይረዳሉ፡፡ስለሆነም ሙስና ወንጀል ነባር ከሚባሉት የወንጀል አይነቶች ልዩ የሚያደርጉት ነጥቦች እንደሚከተለዉ በዝርዝር ቀርበዋል፡፡
3.1 የአፈጻጸሙ ስልት፣
በዋናነት የተለመዱ ወይም ነባር የሚባሉት ወንጀሎች ከፍተኛ ጉጉት ወይም ጥላቻ ዉጤቶች ናቸዉ ማለት ይቻላል፣እነዚህ ወንጀሎች በባህሪያቸዉ ስሜታዊና አብዛኛዉን ጊዜ ሃይልን የሚጠቀሙ ሲሆን ተጠቂዎችም ባብዛኛዉ ግለሰቦች/ቡድኖች ናቸዉ፡፡ ብዙ ጊዜ ከጥላቻ፣ ከቂም በቀል፣ወዘተ ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ደግሞ በቀላሉ ለማጋለጥና ለመመርመር ብሎም አጥፊዎችን ለማስቀጣት ቀላል ነዉ በአንጻሩ የሙስና ወንጀል በሰሜት አልያም በጥላቻ ሳይሆን በሚስጥርና በጥንቃቄ የሚፈጸም ነዉ፡፡በዚህም ምክንያት መፈጸሙን ለማወቅ የሚያስችል ምንም አይነት ምልክት ማግኘት አይቻልም፡፡ከዚህ በተጨማሪም በሚስጥር ወይም በጥንቃቄ መፈጸሙ ብቻ ሳይሆን እጥፊዉ ለምርመራ መነሻ ሊሆን የሚችል አሻራ የማጥፋት አቅም ስላለዉም ከነባር ወንጀሎች ለየት ያደርገዋል፡፡
3.2. በሙስና የተሳተፈ ሁሉ በህግ አይን ወንጀለኛ መሆኑ.
ሙስና ባብዛኛዉ ከአንድ በላይ ስዎችን ያካትታል፣ትስስሩ የሚፈጠረዉ በበላይና በበታች ሰራተኛ ወይም በዉሳኔ ሰጭና በዉሳኔ ተቀባይ መካከል ሊሆን ይችላል፡፡እነዚህ ደግሞ ሚስጥሩን የሚያዉቁ ብቸኛ ሰዎች በመሆናቸዉ ለጥቅማቸዉ ሲሉ ማስረጃ ሊሰጡ አይችሉም፤ ከዚህም በላይ ሁለቱም በህግ አይን ወንጀለኞች በመሆናቸዉ ሚስጥሩን ይገፉበታል እንጅ ለማጋለጥ አይችሉም፣ለዚሀ አባባል የጉቦ ወንጀልን በምሳሌነት መዉሰድ ይቻላል፣ ጉቦ ተቀባይ የተሰጠዉን የስራ ሀላፊነት ወይም የህዝብ አደራ ወደጎን በመተዉ ማድረግ የማይገባዉን በማድረግ ወይም ማድረግ የሚገባዉን ባለድረግ ለጉቦ ሰጭ ጥቅም የሚያሰጥ ዉሳኔ ይሰጣል፣ ጉቦ ሰጭም በምትኩ ላገኘዉ ያልተገባ ጥቅም ገንዘብ ወይም የተለየ ጥቅም ለጉቦ ተቀባይ ይሰጣል፣ እነዚህ ሁለቱም በወንጀሉ ፍሬ ተጠቃሚዎች ከመሆናቸዉም በላይ በህግ አይን ወንጀለኞች ስለሚባሉ ሚስጥሩን ለመደበቅ ይገደዳሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ይህን ወንጀል ለማጋለጥ፣ ለመመርመር እና አጥፊዎችን ለማስቀጣት ይከብዳል፡፡ በአንጻሩ ነባር ወይም መደበኛ በሚባሉ ወንጀሎች አፈጻጸም ላይ እንደዚህ አይነት ትስስር ባለመኖሩ ወንጀሉ የተፈጸመበት ተጎጅ ጉዳት ያደረሰበትን ግለሰብ ለፍትህ አካላት ለመጠቆምና ለማጋለጥ በመቻሉ እንደዚህ አይነት ወንጀሎችን ለመመርመርና ለመክሰስ ልክ እንደሙስና ወንጀል አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ሊኖር አይችልም፡፡

የሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን
የቅጂ መብት © 2016 አኢኢ. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው